SUNDAY, NOVEMBER 4, 2012
ሌሎቹ የጥፋተኝነት ፍርድ የተላለፈባቸው ወልቤካ ለሚ፣ አደም ቡሳ፣ ሀዋ ዋቆ፣ መሐመድ መሉ፣ ደረጀ ከተማ፣አዲሱ ሞክሬና ገልገሎ ጉፋ የተባሉ ግለሰቦች ሲሆኑ፣ የኦነግ አባል በመሆን በተለያዩ ቦታዎች ተማሪዎችእንዲረብሹ፣ ወጣቶችን በመመልመልና ኬንያ ድረስ ወስደው በማሠልጠን በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ መገኘታቸውንናሌሎችንም ድርጊቶች ፈጽመዋል በሚል ዓቃቤ ሕግ የመሠረተባቸውን የሽብርተኝነት ወንጀል ማስተባበልአልቻሉም ተብሎ ነው፡፡
ሁሉም ተከሳሾች የተከሰሱበትን የሽብርተኝነት ወንጀል አለመፈጸማቸውን በመከራከር የመከላከያ ምስክሮችምአቅርበው ያሰሙ ቢሆንም፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት ተከሳሾቹ ዓቃቤሕግ ያቀረበባቸውን ክስና ማስረጃ ማስተባበል አለመቻላቸውን በመግለጽ የጥፋተኝነት ፍርድአስተላልፎባቸዋል፡፡
ጥቅምት 22 ቀን 2005 ዓ.ም. የጥፋተኝነት ፍርድ የተላለፈባቸው ዘጠኙም ተከሳሾች የቅጣት ማቅለያ ሐሳብእንዲያቀርቡ ተጠይቀው ማቅለያ ሐሳብ አቅርበዋል፡፡ አቶ በቀለ ገርባ ባቀረቡት የቅጣት ማቅለያ እንደተናገሩት“ሕይወቴን በሙሉ አድልዎን፣ ኢፍትሐዊነትንና ዘረኝነትን በመቃወም በፈቃዴ ሳይሆን በፈጣሪ ፈቃድ፣ ለኦሮሞሕዝብ ዴሞክራሲና ሰብዓዊ መብቶች መከበር በመታገሌና መስዋዕት በመሆኔ እኮራበታለሁ፤” ብለዋል፡፡በመቀጠልም “ይቅርታ መጠየቅ ካለብኝ የኦሮሞን ሕዝብ በደል በሚገባ ሳልገልጽ ቀርቼ ከሆነ፣ ወንድማማችነትንናአብሮ መኖርን አስቀድሜ ከሆነ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ ለግል ጥቅምና ለዝና ያደረኩትም ካለ እግዚአብሔርንይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ ሳላጠፋ የፈረደብኝን ፍርድ ቤት ቅጣቴን ያቃልልኛል ብዬ ይቅርታ መጠየቅ ባለመፈለጌአዝናለሁ፤” ካሉ በኋላ፣ ባለቤታቸው ከሥራ እንዲወጡ በመደረጋቸው ልጆቻቸው ያለገቢ ለመኖር መገደዳቸውንአስረድተዋል፡፡
ሌሎቹም ተከሳሾች የቤተሰብ ኃላፊ መሆናቸውን፣ በሌላ ወንጀል ተጠይቀው እንደማያውቁ፣ ሕመምተኛመሆናቸውንና ሌሎችንም ያቃልልናል ያሉዋቸውን ሐሳቦች ተናግረው የቅጣት ማቅለያ ሐሳባቸውን አጠቃለዋል፡፡ዓቃቤ ሕግም የቅጣት ማክበጃ ሐሳቡን ካቀረበ በኋላ፣ በጥፋተኞቹ ላይ የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ፍርድ ቤቱለኅዳር 14 ቀን 2005 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ ችሎቱ አብቅቷል፡፡